የአቢሲኒያ መድኃኒት ቤት (The Abyssinian Apothecary) Hard Cover

$33.32
በዓለም ዙሪያ እንልካለን

ለሁሉም ትዕዛዞች ከካርቦን ነፃ መላኪያ።

ቁሳቁሶች እና እንክብካቤ
The Abyssinian Apothecary: Timeless Ethiopian Herbal Remedies for the Modern Kitchen connects traditional wellness practices with modern clinical concepts. Written from the perspective of a clinical pharmacist and functional nutritionist, this guide offers a structured, pharmacy-informed roadmap to safely incorporating Ethiopia's rich botanical heritage into your contemporary cooking and daily routine. It replaces historical ambiguity with practical kitchen applications, empowering you to explore ancestral traditions alongside modern clinical insights. Why This Book is Unique While most herbal guides focus strictly on standalone plants, this book delivers an educational blueprint focused on two core areas: The Concept of Herbal Synergy: Instead of analyzing plants in isolation, it explores how traditional Ethiopian practices combine specific herbs, detailing the logic of how certain botanicals complement one another. The Clinical Pharmacist's Safety Lens: Prioritizing a safety-first approach, every remedy includes clear guidance on step-by-step preparation, storage, and conservative serving suggestions. Crucially, it highlights vital safety parameters, including potential herb-drug interactions and specific warnings for individuals taking medications, managing chronic conditions, or who are pregnant/nursing. “የአቢሲኒያ መድኃኒት ቤት” የጥንቶቹን የባህል ሕክምና ልምዶች ከዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ ጋር ያገናኛል። መጽሐፉ በክሊኒካል ፋርማሲስት እና በአመጋገብ (Nutrition) ባለሙያ ዕይታ የተዘጋጀ በመሆኑ፣ የሀገራችንን የበለጸገ የዕፅዋት ቅርስ በዕለት ተዕለት ምግብ አዘገጃጀትዎ ውስጥ እንዴት በደኅንነት መጠቀም እንደሚችሉ ግልጽና ሥርዓት ያለው መመሪያ ይሰጣል። ግራ የሚያጋቡ የድሮ አባባሎችን በማስቀረት፣ በቀጥታ በኩሽናዎ ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉ መፍትሔዎችን በማቅረብ የድሮ አያቶቻችንን ጥበብ በዘመናዊ ሳይንሳዊ መንገድ እንዲረዱ ያደርግዎታል። ይህ መጽሐፍ ምን ልዩ ያደርገዋል? አብዛኛዎቹ የዕፅዋት መመሪያዎች ትኩረት የሚያደርጉት በአንድ ተክል እና በብቸኛ ጥቅሙ ላይ ብቻ ነው። ይህ መጽሐፍ ግን በሁለት ዋና ዋና ነገሮች ላይ በማተኮር የተለየ መንገድ ያሳያል፦ የዕፅዋት ቅንጅት (Herbal Synergy)፦ እፅዋትን ለብቻቸው ከማየት ይልቅ፣ የኢትዮጵያ የባህል ሕክምናዎች የተለያዩ እፅዋትን እንዴት አዋህደው እንደሚጠቀሙ ያብራራል። የተመረጡት እፅዋት እርስ በእርስ እንዴት እንደሚደጋገፉና ጥንካሬያቸውን እንደሚያሳድጉ በምክንያት ያሳያል። የፋርማሲስት የደኅንነት ጥንቃቄ፦ ለደኅንነትዎ ቀዳሚ ትኩረት በመስጠት፣ እያንዳንዱ መፍትሔ ደረጃ በደረጃ እንዴት እንደሚዘጋጅ፣ እንዴት እንደሚቀመጥና መጠኑ ምን ያህል መሆን እንዳለበት ግልጽ መመሪያ አካቷል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እፅዋቱ ከሚወሰዱ ሌሎች ዘመናዊ መድኃኒቶች ጋር ሊያመጡ የሚችሉትን መስተጋብር (Interactions) እንዲሁም መድኃኒት የሚወስዱ፣ ሥር የሰደደ ሕመም ያለባቸው ወይም ነፍሰ ጡርና አጥቢ እናቶች ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው በዝርዝር ያስረዳል።
ጭነት እና ተመላሽ

የማጓጓዣ ወጪ በክብደት ላይ የተመሰረተ ነው። ምርቶችን ወደ ጋሪዎ ያክሉ እና የመላኪያ ወጪውን ለማየት የማጓጓዣ ካልኩሌተርን ይጠቀሙ።

በግዢዎ 100% እርካታ እንዲሰማዎት እንፈልጋለን። እቃዎች ከደረሱ በ30 ቀናት ውስጥ ሊመለሱ ወይም ሊለዋወጡ ይችላሉ።